ኤግዚቢሽኑ በውሃና ኢነርጂ ዘርፍ ተግባራት ዙሪያ ዜጎች በቂ ግንዘቤ እንዲይዙ ይረዳል - የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ - መነሻ - am
ネスティッドポートレット
アセットパブリッシャー
Statistics
× አድራሻ: ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስኩየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር
Webコンテンツの検索
アセットパブリッシャー
ሀገር አቀፍ የውሃና ኢነርጂ ኤግዚቢሺን በብሄራዊ ሳይንስ ሙዚየም በዛሬው ዕለት በይፋ መጎብኘት ጀምሯል፡፡
በመርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ መድረክ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ በዘርፉ በተሰሩ ስራዎች ዙሪያ ዜጎች በቂ ግንዘቤ እንዲይዙ ያግዛል ብለዋል፡፡
በመንግስትና አጋር አካላት በርካታ የልማት ስራዎች ስለመከናወናቸው የተናገሩት ሚኒስትሩ በተለይ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የታየው የልማት እንቀስቃሴ ለአብነት ተጠቃሽ ነው ብለዋል፡፡
በመሆኑም ዜጎች በውሃና ኢነርጂ ተግባራት ቀጥተኛ ተሳታፊና ተጠቃሚ በመሆናቸው በብሄራዊ ሳይንስ ሙዚየም ተገኝተው ኤግዚቢሺኑን እንዲጎበኙም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ኤግዚቢሺኑ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አዘጋጅነት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት፣ የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ፣ የኢትዮጵያ ውሃ ተክኖሎጂ ኢንስትቲዩት እንዲሁም በውሃና ኢነርጂ ዘርፍ የተሰማሩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የተሳተፉበት ስለመሆኑም ተገልጿል፡፡
ネスティッドポートレット
アセットパブリッシャー
— ページごとの項目数 5