የሕዳሴው ግድብ ሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሌት በዓባይ የውኃ መጠን ላይ ተፅዕኖ አለመፍጠሩን ሱዳን ገለጸች - መነሻ - am
ネスティッドポートレット
アセットパブリッシャー
Statistics
× አድራሻ: ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስኩየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር
Webコンテンツの検索
アセットパブリッシャー
የሕዳሴው ግድብ ሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሌት ጋር ተያይዞ በዓባይ የውኃ መጠን ላይ ተፅዕኖ አለመፈጠሩን የሱዳኑ አል-ሩሳሬስ ግድብ ዋና ዳይሬክተር ሐሚድ ሞሐመድ ዓሊ አስታወቁ።
ሐሚድ ሞሐመድ ዓሊ እሁድ ዕለት በሰጡት መግለጫ፣ ኢትዮጵያ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሌት ብትጀምርም በጥቁር ዓባይ የውኃ ፍሰት ላይ የጠብታ ያህል እንኳን ልዩነት አልታየም ብለዋል።
"በኢትዮጵያ አዋሳኝ ድንበር ላይ የሚገኘው አል-ዴይም ጣቢያ ከፈረንጆቹ ሚያዝያ ወር ጀምሮ ከኢትዮጵያ ወደ ሱዳን በሚፈስሰው የውኃ መጠን ላይ አንዲትም የጠብታ መቀነስ አዝማሚያ አላገኘም" ነው ያሉት።
የግድቡ ሁለተኛ የውኃ ሙሌት እየተከናወነ ቢሆንም በየዕለቱ ወደ ሱዳን የሚፈስሰው የውኃ መጠን አለመቀነሱን ነው የገለጹት።
ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ የሕዳሴውን ግድብ የውኃ ሙሌት ብታከናውንም የግድቡን የውኃ ሙሌት እና አሠራር በተመለከተ አሁንም ቢሆን ሕጋዊ እና አስገዳጅ ስምምነት መፈረም አለበት ሲሉ መናገራቸውን ሽንዋ ዘግቧል።
ネスティッドポートレット
アセットパブリッシャー
— ページごとの項目数 5