Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

アセットパブリッシャー

በሱማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ የተመራው ልኡካን ቡድን ሀገር አቀፍ የውሃና ኢነርጂ ኤግዚቢሽንን ጎበኘ

የሱማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ የተመራ ልኡካን ቡድን ሀገር አቀፍ የውሃና ኢነርጂ ኤግዚቢሽንን ተዘዋውሮ ጎብኝቷል ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በሳይንስ ሙዝየም የተዘጋጀውን የውሃ እና ኢነርጂ ኤግዚብሽን በጎበኙበት ወቅት በዘርፉ እንደ ሀገር የተሰሩ ስራዎችን አድንቀዋል ።

የሱማሌ ክልል ከፍተኛ የውሃ እጥረት ከሚስተዋልባቸው አከባቢዎች አንዱ በመሆኑ በክለሉ የለውን የውሃ ሃብት በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ የተናግሩት ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ የዉሃና ኢነርጂ ልማት ተግባራትን በቴክኖሎጂ አስተሳስሮ የመጠቀም ልምዶችን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መቅሰም እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።

በጉብኝቱ ወቅት ለልኡካን ቡድኑ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሂደት የተከናወኑ ተግባራትና የታየው ህዝባዊ ተሳትፎ ዙሪያ ገለጻ የተደረገላቸው ሲሆን በvirtual Reality (VR) አማካኝነት ግድቡ የደረሰበት አሁናዊ ደረጃም ተጎብኝቷል፡፡