የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ለህዳሴ ግድብ ግንባታ እስካሁን ከ205 ሚሊዮን ብር በላይ የቦንድ ግዥ መፈፀሙን አስታወቀ *********** - መነሻ - am

פורטלטים מקוננים

מוציא לאור של הנכס

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ ו, 17 יונ 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች ד, 8 יונ 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ ד, 8 יונ 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

מוציא לאור של הנכס

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ለህዳሴ ግድብ ግንባታ እስካሁን ከ205 ሚሊዮን ብር በላይ የቦንድ ግዥ መፈፀሙን አስታወቀ ***********

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ድረስ ከ205 ሚሊዮን ብር በላይ የቦንድ ግዥ መፈፀሙን አስታውቋል።
የህዳሴ ዋንጫውን ከኢፌዴሪ መከላከያ ተረከቦ ለሳምንታት የተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ስራዎችን ሲሰራ የቆየው የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከያ ዘርፍ በዛሬው እለት የታላቁ ህዳሴ ዋንጫን ለወንጀል ምርመራ ዘርፍ በአዲስ አበባ ወዳጅነት አደባባይ አስረክቧል።
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከያ ዘርፍ ባለፉት ቀናት ለታላቁ ህዳሴ ግድብ 12 ሚሊዮን ብር ማሰባሰቡን አስታውቋል።
ኮሚሽኑ ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ ለ7 ዓመታት ባከናወናቸው ስራዎች ከ205 ሚሊዮን ብር በላይ የቦንድ ግዥ መፈፀሙንም ነው ያስታወቀው።
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚነር ጄኔራል መላኩ ፋንታ በዋንጫ ርክክብ ስነ-ስርዓቱ ወቅት ባስተላለፉት መልእክት ለዘመናት የህዝቦች ህልም የነበረውን ታላቁን ህዳሴ ግድብ እውን ሚሆንበት ጊዜ ላይ መሆናችን ወቅቱን ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።
ፕሮጀክቱ የሁሉም ህብረተስብ አሻራ ያረፈበት ነው ያሉት ም/ል ኮሚሽነሩ ፕሮጀክቱን ከዳር ለማድረስም ሁሉም ኢትዮጵያውያን በላቀ ትብብር መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
ፌዴራል ፖሊስ የታላቁ ህዳሴ ግድብ የመሰረት ድንጋይ ከተጣለበት ጊዜ አንስቶ ከማንኛውም ዓይነት ጥቃት ለመመከት አስተማማኝ ጥበቃ እያደረገና ህዝቡ የጣለበትን ኃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑንም ም/ል ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።
በሀገሪቱ በተለያዩ አከባቢዎች ያሚገኙ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ደህንነት በመጠበቅ ረገድ የፌዴራል ፖሊስ ሀገራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ላይ ይገኛልም ነው ያሉት።
በመርሃ ግብሩ የኮሚሽኑ ከፍተኛ ኃላፊዎች እና ሌሎች የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ምንጭ፡- ኢቢሲ

פורטלטים מקוננים

מוציא לאור של הנכס

— פריטים לדף
מציג 1 - 5 מתוך 16 תוצאות.