ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ከጠ/ሚ ዐቢይ የተላከ ደብዳቤን ለኡጋንዳው ፕሬዚዳንት አደረሱ - መነሻ - am

פורטלטים מקוננים

מוציא לאור של הנכס

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ ו, 17 יונ 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች ד, 8 יונ 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ ד, 8 יונ 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

מוציא לאור של הנכס

ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ከጠ/ሚ ዐቢይ የተላከ ደብዳቤን ለኡጋንዳው ፕሬዚዳንት አደረሱ

የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተላከ ደብዳቤን ለዑጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ አደረሱ፡፡
በሚኒስትሩ የተመራ ልዑክ ከፕሬዚዳንቱ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል፡፡
በዚህ ወቅት ሚኒስትሩ በመጪው ሃገራዊ ምርጫ፣ በታላቁ የህዳሴ ግድብ፣ በትግራይ ክልል እየተደረገ ስላለው ሰብአዊ ድጋፍና የመልሶ ማቋቋም እንዲሁም በኢትዮ ሱዳን የድንብር ውዝግብ ጉዳይ ለፕሬዚዳንቱ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
የኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ በበኩላቸው የናይል ተፋሰስ ሃገራት ከወንዙ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ ባሉ ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር በስብሰባ መልክ ጉባኤ ጠርተው እንዲወያዩ ሃሳብ አቅርበዋል፡፡
በሚኒስትሩ የተመራ ልዑክ ባለፈው ሳምንት ለደቡብ ሱዳን እና ሩዋንዳ መሪዎች ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተላከ ደብዳቤን ማድረሱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
ምንጭ፡- ኤፍ ቢ ሲ ፤ሰኔ 4 ፣ 2013

פורטלטים מקוננים

מוציא לאור של הנכס

— פריטים לדף
מציג 1 - 5 מתוך 16 תוצאות.