ግድቡ በመጭው ክረምት የቅድመ ምርት እንደሚጀምር ተገለጸ - መነሻ - am

פורטלטים מקוננים

מוציא לאור של הנכס

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ ו, 17 יונ 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች ד, 8 יונ 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ ד, 8 יונ 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

מוציא לאור של הנכס

ግድቡ በመጭው ክረምት የቅድመ ምርት እንደሚጀምር ተገለጸ
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በመጭው ክረምት የቅድመ ምርት እንደሚጀምር ተገለጸ፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከተለያዩ የሃይማኖት ተቋማትና ሲቪክ ማህበራት ጋር በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ተወያይቷል፡፡
በውይይቱ ላይ ግድቡ በክረምቱ የቅድመ ምርት እንደሚጀመር የተገለጸ ሲሆን፥ ለዚህ የሚያግዝ የ650 ኪሎ ሜትር መስመር ዝርጋታ ተከናውኗል ነው የተባለው፡፡
ከዚህ ባለፈም ግድቡ በመጭው ክረምት 18 ነጥብ 4 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ እንደሚይዝም በመድረኩ ተነስቷል፡፡
በውይይቱ ላይ የሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት ወቅቱን ጠብቆ እንደሚከናወንም ነው የተገለጸው፡፡
አሁን ላይ የግድቡ ግንባታ 80 በመቶ የደረሰ ሲሆን፥ የሲቪል ስራው 91 ነጥብ 8 በመቶ፣ የኤሌክትሮ መካኒካል 54 ነጥብ 5 በመቶ እንዲሁም ሃይድሮሊክ ስትራክቸር 55 ነጥብ 2 በመቶ መድረሱ ተገልጿል፡፡
የግድቡ መጠናቀቅም የሃገሪቱን የኢነርጅ ሃይል በሰአት ከ73 ኪሎ ዋት ወደ 220 ኪሎ ዋት ያሸጋግረዋል ተብሏል፡፡
የግድቡን የሙሌት ሂደት ለማደናቀፍ የሚደረጉ ጥረቶችን፣ የኦፕሬሽን እና የውሃ አለቃቀቅ ሂደቶችን ኢትዮጵያ ፈጽሞ አትቀበልምም ነው የተባለው፡፡
የሃይማኖትና የሲቪክ ማህበራቱም ለግድቡ እውን መሆን እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡
በብስራት መለሰ
ኤፍ ቢ ሲ

פורטלטים מקוננים

מוציא לאור של הנכס

— פריטים לדף
מציג 1 - 5 מתוך 16 תוצאות.