ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ገቢ ማሰባሰቢያ ንቅናቄ በአዲስ አበባ ተጀመረ - መነሻ - am

פורטלטים מקוננים

מוציא לאור של הנכס

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ ו, 17 יונ 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች ד, 8 יונ 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ ד, 8 יונ 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

מוציא לאור של הנכס

ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ገቢ ማሰባሰቢያ ንቅናቄ በአዲስ አበባ ተጀመረ

ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ገቢ ማሰባሰቢያ በአዲስ አበባ ከተማ ተጀመረ።

“ግድባችን የአንድነታችን እና የሉአላዊነታችን መገለጫ ነው” በሚል መሪ ቃል የገቢ ማሰባሰቢያ እና የንቅናቄ ስራ በከተማዋ በ11ም ክፍለ ከተሞች ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት እና የኢትዮጵያ ታሪክ ባህልና ቅርስ አድን ድርጅት አዘጋጅነት የተጀመረው መርሃግብር ህብረተሰቡን በማነቃነቅ ለግድቡ የሞራልም ሆነ የገንዘብ ተሳትፎ እንዲያደርግ ለማስቻል መሆኑን ከከተማዋ ፕሬስ ሴክሪታሪያት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ታሪክ እና ቅርስ እንደመሆኑ ይህንን በማስተዋወቅ በመጪው ሀምሌ ወር ለሚደረገው ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት ህብረተሰቡ የበኩሉን ድጋፍ እና ተሳትፎ እንዲያደርግ ከወዲሁ ለማነሳሳት መሆኑን የመርሃግብሩ አዘጋጆች ገልጸዋል፡፡

˝የህዳሴ ግድብ ጎዞ "በሚል በሀገር አቀፍ ደረጃ በተካሄደ የንቅናቄ እና የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር በ32 ከተሞችና በ200 ወረዳዎች ከ11 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰብ የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ደጀኔ ገ/ማርያም ገልጸዋል፡፡

ኤፍ.ቢ.ሲ

פורטלטים מקוננים

מוציא לאור של הנכס

— פריטים לדף
מציג 1 - 5 מתוך 16 תוצאות.