ግብፅ እና ሱዳን የአፍሪካ ህብረት የተሰጠውን ሃላፊነት የሚያንኳስስ ሙከራ ማድረጋቸው ተቀባይነት የለውም - ኢንጂነር ስለሺ - መነሻ - am

פורטלטים מקוננים

מוציא לאור של הנכס

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ ו, 17 יונ 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች ד, 8 יונ 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ ד, 8 יונ 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

מוציא לאור של הנכס

ግብፅ እና ሱዳን የአፍሪካ ህብረት የተሰጠውን ሃላፊነት የሚያንኳስስ ሙከራ ማድረጋቸው ተቀባይነት የለውም - ኢንጂነር ስለሺ

ግብፅ እና ሱዳን የአፍሪካ ህብረት የተሰጠውን ሃላፊነት የሚያንኳስስ ሙከራ ማድረጋቸው ተቀባይነት እንደሌለው የውሃ፣ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ገለጹ፡፡

ሚኒስትሩ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መዲና ኪንሻሳ ስለተደረገው የሶስቱ ሀገራት የውጭ ጉዳይና የውሃ ሚኒስትሮች ውይይት በሰጡት መግለጫ፥ ካይሮ እና ካርቱም ድርድሩን የማጓተት ስትራቴጂን በመከተላቸው ሰፊ ጊዜ ጠፍቷል ብለዋል።

ደቡብ አፍሪካ ከታዛቢነት እንድትወጣ የቀረበው ሀሳብም የአፍሪካ ህብረትን ክብር የማይመጥን ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የሀገራቱ የድርድሩን ቅርጽ የመለወጥ እና ከይዘት ይልቅ ሂደት ላይ ማተኮር በኪንሻሳው ስብሰባ ላይ መታየቱንም ነው ሚኒስትሩ የጠቆሙት።

በመግለጫቸው ኢትዮጵያ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል ድርድሩ በፍጥነት እንዲጠናቀቅ የአባይን ውሃ ምክንያታዊ እና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ የመጠቀም ሉዓላዊ መብቷን እንዳስረዳችም ገልጸዋል።

ከትብብር ይልቅ የአንድ ወገን ተጠቃሚነትን ለሚያረጋግጥ ሃሳብ ምንም አይነት ቦታ እንደሌላትም ሚኒስትሩ በመግለጫቸው ያነሱት።

ከግድቡ ውሃ ሙሌትም ይሁን ከአጠቃላይ የግድቡ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ጠቃሚ መረጃዎችን ለመለዋወጥ ዝግጁነቷን በመጥቀስም፥ ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት በተያዘለት ጊዜ እንደሚካሄድ አስረድተዋል።

ከሱዳን በኩል እየተነሱ ያሉ ወቀሳዎችም ምንም አይነት መሰረት የሌላቸው መሆኑን በኪንሻሳው ስብሰባ በስፋት ማስረዳታቸውንም አውስተዋል።

ግብፅ ድጋፍ የቸረችው የሱዳን ድርድሩን የማጓተቻ ሀሳቦች ከታዛቢዎች ጋር የተያያዙ እና የድርድሩን ቅርጽ የመለወጥ እንቅስቃሴዎች ተቀባይነት የሌላቸው መሆኑንም ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል።

በመጨረሻም ታዛቢ ተብለው የተመረጡት ደቡብ አፍሪካ፣ አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት አዎንታዊ ሚናቸው ጨምሮ በታዛቢነታቸው እንዲቀጥሉ ስምምነት ላይ መደረሱንም ተናግረዋል።

ሃገራቱ የሚያደርጉት የሶስትዮሽ ድርድር በስምንት ሳምንታት እንዲጠናቀቅ ነው የታሰበ ሲሆን፥ ቀጣዩ ድርድርም የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት በሚሰጡት አቅጣጫ ይወሰናል ተብሏል፡፡

በኤፍ ቢ ሲ

פורטלטים מקוננים

מוציא לאור של הנכס

— פריטים לדף
מציג 1 - 5 מתוך 16 תוצאות.