ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቷን አልምታ የመጠቀም ሙሉ መብት አላት -ፕሮፌሰር ተስፋዬ ታፈሰ - መነሻ - am

פורטלטים מקוננים

מוציא לאור של הנכס

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ ו, 17 יונ 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች ד, 8 יונ 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ ד, 8 יונ 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

מוציא לאור של הנכס

ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቷን አልምታ የመጠቀም ሙሉ መብት አላት -ፕሮፌሰር ተስፋዬ ታፈሰ

ኢትዮጵያ በሉዓላዊ ግዛቷ ውስጥ የሚገኘውን የተፈጥሮ ሀብቷን አልምታ የመጠቀም ሙሉ መብት እንዳላት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፖለቲክስና የአፍሪካ ጥናት ማዕከል መምህርና ተመራማሪ ከሆኑት ፕሮፌሰር ተስፋዬ ታፈሰ አስታወቁ፡፡

በዓባይ ወንዝ ላይ የተለያዩ ጥናቶችን ያደረጉት ፕሮፌሰር ተስፋዬ ÷ በዓባይ ወንዝ ውሃ አጠቃቀም ዙሪያ ሱዳንና ግብጽ የያዙት አቋም የተሳሳተ ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአንፃሩ የራሷን የተፈጥሮ ሀብት ሌሎችን በማይጎዳ መልኩ ለመጠቀም የምታደርገው ጥረት የሚደነቅ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ማንኛውም ሉዓላዊ ሃገር ያለውን የተፈጥሮ ሀብት ያለማንም ከልካይነት አልምቶ የመጠቀም ሙሉ መብት እንዳለው የሚያስረዱት ፕሮፌሰር ተስፋዬ÷ ኢትዮጵያም የዓባይን ውሃ በመገደብ ሌሎችን በማይጎዳ መልኩ መገልገል እንደምትችልና ይህን ለማድረግ ሙሉ መብት እንዳላት ተናግረዋል፡፡

የታችኛው ተፋሰስ ሃገራት ሱዳንና ግብጽ የዓባይ ውሃ አጠቃቀምን በተመለከተ የኢትዮጵያን ጥቅም ባላከበረ መልኩ ከዚህ ቀደም የተለያዩ ስምምነቶች ማድረጋቸውን አስታውሰዋል።

ሁለቱ ሃገራት የውሃውን ድርሻ ተገቢ ባልሆነ መልኩ መከፋፈላቸውንም አመልክተዋል፡፡

ክፍፍሉ ዋነኛዋ የውሃው መነሻና 86 ከመቶ የውሃ ድርሻ የምታበረክተውን ኢትዮጵያንም ሆነች ሌሎች የላይኛው የተፋሰሱ ሃገራትን ያላካተተ በመሆኑ የሁለቱ ሃገራት ስምምነት ተቀባይነት እንደሌለው አስታውቀዋል፡፡

የግብጽ መሪዎች በተደጋጋሚ ከድርሻችን አንዲት ጠብታ ውሃ እንዲነካብን አንፈቅድም ሲሉ መሰማታቸውን የሚገልፁት ፕሮፌሰር ተስፋዬ÷ ሃገራቱ ድርሻችን የሚሉት የተሳሳተ እሳቤ ውጤት መሆኑን ማመልከታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

ኤፍ ቢ ሲ

פורטלטים מקוננים

מוציא לאור של הנכס

— פריטים לדף
מציג 1 - 5 מתוך 16 תוצאות.