የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህልውና ለመጠበቅ በተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ ሥራ ላይ ሁሉም አካል ርብርብ ሊያደርግ እንደሚገባ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሳሰቡ - መነሻ - am
פורטלטים מקוננים
מוציא לאור של הנכס
Statistics
× አድራሻ: ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስኩየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር
חיפוש בתוכן אינטרנט
מוציא לאור של הנכס
የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህልውና ለመጠበቅ በተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ ሥራ ላይ ሁሉም አካል ርብርብ ሊያደርግ እንደሚገባ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሳሰቡ
ታህሳስ 25: 2013
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ህልውና ለመጠበቅ በተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ ሥራ ላይ ሁሉም አካል ርብርብ ሊያደርግ እንደሚገባ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር አሳሰቡ፡፡
የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የ2013 ዓ.ም የበጋ የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ ሥራ እንዲሁም ያለፉትን ዓመታት የሥራ ክንውን እውቅና የሚሰጥበት የንቅናቄ መድረክ በባሕር ዳር እያካሄደ ነው፡፡
በመድረኩ ላይ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከመገንባት ባሻገር ለህልውናውም ማሰብ ተገቢ ነው ብለዋል፡፡
ግድቡ በደለል እዳይሞላ የተፈጥሩ ሀብት ልማትና ጥበቃ ሥራን በጥራትና በስፋት ማካሄድ እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ አስገንዝበዋል፡፡
በእንቦጭ አረም ምክንያት አደጋ ላይ የወደቀዉን ጣና ሐይቅ ለመታደግ አረሙን ነቅሎ ማስወገድ ብቻ መፍትሄ ባለመሆኑ በደለል እንዳይሞላ የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ ሥራ በየአካባቢው ማከናወን ይገባል ብለዋል፡፡
የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኀላፊ ዶክተር መለሰ መኮንን በዘንድሮው የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ ሥራ የሚሳተፉ አካላት ሥራዉ ዘላቂ እንዲሆን በባለቤትነት ትኩረት ሰጥተው እንዲሠሩ መጠየቃቸውን አብመድ ዘግቧል።
פורטלטים מקוננים
מוציא לאור של הנכס
— פריטים לדף