ከታላቁ ኅዳሴ ግድብ ኃይል ለማመንጨት ዝግጅቱ እየተገባደደ ነው - መነሻ - am
פורטלטים מקוננים
מוציא לאור של הנכס
Statistics
× አድራሻ: ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስኩየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር
חיפוש בתוכן אינטרנט
מוציא לאור של הנכס
ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ግንባታ የመጀመሪያ ዙር ኃይል ማመንጨት በሚያስችል ደረጃ እየተገባደደ መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ለዋልታ ገለፁ፡፡
ግድቡ ተጠናቆ ለታለመለት ዓላማ እንዳይውል የሚሹ የውጭ ኃይሎች ተላላኪያቸው የሆነውን አሸባሪው ትሕነግ በመጠቀም ለማደናቀፍ ቢጥሩም በመላው ኢትዮጵያዊያን ቁርጠኝነት የታላቁ ኅዳሴ ግድብ ግንባታ ወደ መጠናቀቁ ምዕራፍ እየሄደ መሆኑን አሳውቀዋል፡፡
በኢትዮጵያ ላይ እየደረሰ ያለው ጫና መላው ኢትዮጵዊያንን ቁጭት ውስጥ የከተተ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ሀብታሙ (ዶ/ር) የኅዳሴ ግድቡ ግንባታ ላይ የሚሰሩ ኢትዮጵያዊያንም በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ውስጥ ሆነው በከፍተኛ ወኔና በቁጭት 24 ሰዓት እየሰሩ ነው ብለዋል፡፡
ጠላትን ማሸነፍ የሚቻለው በጦር ግንባር ብቻ አይደለም ያሉት ሚኒስትሩ የልማት ሥራዎችን በተገቢው መንገድ በማጠናቀቅና የአገሪቱን ብልጽግና በማረጋገጥ ድልን መጎናፀፍ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ሚኒስትሩ ከዋልታ ጋር ባደረጉት ቆይታ መላውኢትዮጵያዊያን ለግድቡ ግንባታ የሚችሉትን ሁሉ ድጋፍ እያደረጉ ነው ያሉም ሲሆን አሁንም የሚደረገውን ድጋፍ በማጠናከር ግድቡ ተጠናቆ የሚሰጠውን የኃይል ጥቅም መቋደስ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
(ዋልታኅዳር 27/2014
פורטלטים מקוננים
מוציא לאור של הנכס
— פריטים לדף