የታላቁ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ኢትዮጵያን በተለያዩ መስኮች ከፍ እንድትል ያደርጋል-ምሁራን - መነሻ - am
פורטלטים מקוננים
מוציא לאור של הנכס
Statistics
חיפוש בתוכן אינטרנט
מוציא לאור של הנכס
የታላቁ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ኢትዮጵያን በተለያዩ ዘርፎች ከፍ እንድትል የሚያስችላት መሆኑን የውሃ ጉዳይ ተመራማሪና የምጣኔ ሃብት ምሁራን ገለጹ፡፡
በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና አለም አቀፍ ግንኙነት መምህርና የውሃ ጉዳዮች ተመራማሪው ዶክተር ውብእግዜር ፈረደ እንደሚሉት÷ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ወደ ስራ መግባት አዲስ የታሪክ ምዕራፍን የሚከፍት ነው፡፡
ኢትዮጵያ በቀጠናው ጂኦ-ፖለቲካ ያላትን ተደማጭነት በማሳደግ ረገድ ያለው ሚና ከፍ እንደሚልም ነው ተመራማሪው የጠቆሙት፡፡
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የምጣኔ ሃብት ባለሙያ እንዲሁም የሶሾ-ኢኮኖሚ ጉዳዮች ተንታኙ አቶ ዋሲሁን በላይ በበኩላቸው÷ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ማነቆ ለሆነው የሃይል አቅርቦት ታላቁ የህዳሴ ግድብ ይዞት የሚመጣው ትሩፋት ከፍ ያለ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በቂ የሆነ የሃይል አቅርቦትም አዳዲስ የቢዝነስ ዘርፎች እንዲተዋወቁ በማድረግ ረገድ የሚኖረው አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሚሆን አንስተዋል፡፡
የፕሮጀክቱ እውን መሆን ሌሎች አቅሞችን በማሳደግ ተጨማሪ ሃገራዊ ፕሮጀክቶችን እውን ለማድረግ እንደሚያግዝም ምሁራኑ አስረድተዋል፡፡
ታላቁ የህዳሴ ግድብን ለማጠናቀቅ ብሎም አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ለመገንባትም አንድነትን ማጠናከር እና የተጀመሩ የትብብር ስራዎችን ማነቃቃት እንደሚጠበቅ አሳስበዋል፡፡
ምንጭ፡- ኤፍ ቢ ሲ፣ ሰኔ 18 ፣ 2013