በአፍሪካ ህብረት አማካኝነት የሚካሄደው የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር በዚህ ሳምንት መጨረሻ ይቀጥላል - ዶክተር ስለሺ በቀለ - መነሻ - am
Conteneur d'applications
Agrégateur de contenus
Statistics
× አድራሻ: ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስኩየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር
Recherche de contenu Web
Agrégateur de contenus
በአፍሪካ ህብረት አማካኝነት የሚካሄደው የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር በዚህ ሳምንት መጨረሻ ይቀጥላል - ዶክተር ስለሺ በቀለ
የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚንስትር ዶክተር ስለሺ በቀለ በአፍሪካ ህብረት አማካኝነት የሚካሄደው የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር በዚህ ሳምንት መጨረሻ እንደሚደረግ አስታወቁ፡፡
ድርድሩ በአዲሷ የህብረቱ ሊቀመንበር በሆነችው በዲሞክራቲክ ኮንጎ ሪፓብሊክ አወያይነት ነው የሚካሄደው፡፡
ድርድሩ የሚካሄደው ዲሞክራቲክ ኮንጎ ለሦስቱ ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችና የውሃ ሚኒስትሮች ባቀረበችው ጥያቄ መሰረት መሆኑን ዶክተር ስለሺ በቀለ ገልጸዋል፡፡
የህበረቱ ባለሙያዎች፣ ታዛቢዎች እና የሦስቱ ሃገራት ባለሙያዎች በድርድሩ ላይ እንደሚገኙ ይጠበቃል፡፡
ሚኒስትሩ አባይ ድንበር ተሻጋሪ የውሃ ሃብት መሆኑን ጠቅሰው የህዳሴ ግድቡ ትልቅ የኃይል ምንጭ ይሰጣመሆኑንም አስታውሰዋል፡፡
የኃይል አቅርቦቱን ከማሳደግ በተጨማሪም ልማትን የሚደግፍ ነው ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡
ኢትዮጵያ የውሃ ሃብቱን ጉልህ ጉዳት ሳያስከትል በመርህ ላይ የተመሰረት ፍትሃዊ እና ምክንያታዊ አጠቃቀም ላይ ቁርጠኛ የሆነ አቋም እንዳላት ነው ሚኒስትሩ ያስታወቁት፡፡
Conteneur d'applications
Agrégateur de contenus
— Articles par la page