በኤግዚቢሺኑ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሂደት እየተጎበኘ ይገኛል - መነሻ - am
Sisällytetyt portletit
Sisältöjulkaisija
Statistics
× አድራሻ: ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስኩየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር
Web-sisällön haku
Sisältöjulkaisija
ሀገር አቀፍ የውሃና ኢነርጂ ኤግዚቢሺን በብሄራዊ ሳይንስ ሙዚየም በዛሬው ዕለት በይፋ መከፈቱን ተከትሎ በርካታ ጎብኝዎች ታድመዋል፡፡
በጉብኝቱም የሰንደቅዓላማ ፕሮጀክት የሆነው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ፣ ከቁጭት ወደ ልማት የተሸጋገረበት ሂደት፣ የኢትዮጵያውያንና ትውለደ እትዮጵያውያን ዘርፈ ብዙ ድጋፍና የሀብት አሰባሰብ ውጤት ለዕይታ ቀርቧል፡፡
በመርሃ ግብሩ የታላቁ ህዳሴ ግድብ አሁናው የግንባታ ሂደትን በርካቶች በ3ዲ ምስለ ጉብኝት በመታገዝ እየተመለከቱት ሲሆን ታዳጊ ሕፃናትም እየተዝናኑ ስለህዳሴ ግድብ ያላቸውን እውቀት ከፍ የሚያደርጉበት ፐዝል ተዘጋጅቶ የህዳሴን ግድብ የመገጣጣም አዝናኝና አስተማሪ የሆነ ተግባር ሲከውኑ ውለዋል፡፡
በጉብኝቱ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ እንዲሁም ከተለያዩ የመንግስት ተቋማት ተጋብዘው የተገኙ የመንግስት ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች፣ ተመራማሪዎች፣ ምሁራና ሌሎች በርካታ ጎበኚዎች ተሳትሰዋል፡፡
Sisällytetyt portletit
Sisältöjulkaisija
— Merkintöjä per sivu