በዶሃ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለህዳሴ ግድብ የቦንድ ግዢ ፈጸሙ - መነሻ - am
Sisällytetyt portletit
Sisältöjulkaisija
Statistics
× አድራሻ: ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስኩየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር
Web-sisällön haku
Sisältöjulkaisija
ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በዶሃ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም የዳያስፖራ ማህበራት የ25 ሺህ የአሜሪካን ዶላር የቦንድ ግዥ ፈጽመዋል።
በቀጠር የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ማህበር የ15 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ዋጋ ያለው የቦንድ ግዥ በያዝነው ሳምንት ፈፅሟል።
የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሳሚያ ዘካሪያ የቦንድ ግዥውን ለፈፀሙ አካላት የቦንድ ሰርተፍኬት ርክክብ ያደረጉ ሲሆን፥ ዜጎች በዚህ ወሳኝ ወቅት ለግድቡ እያሳዩት ያለው ቀጣይነት ያለው ድጋፍ የሚደነቅ መሆኑንም ተናግረዋል።
ሌሎችም ይህንኑ አርዓያነት ያለው ተግባር እንዲደግፉ አምባሳደሯ ጥሪ ማቅረባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ኤምባሲው የቦንድ ግዥ በመፈጸም እና በሌሎች ድጋፎች የተሳተፉ ዜጎችን፣ የህዳሴ ግድብ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን አባላት እና የዳያስፖራ አደረጃጀቶችን አመስግኗል።
ኤፍ ቢ ሲ፣ ሃምሌ 1/ 2013
Sisällytetyt portletit
Sisältöjulkaisija
— Merkintöjä per sivu