የናይል ተፋሰስ ሀገራት የሚሳተፉበት የሴካፋ ውድድሩ ለህዳሴው ግድብ ገጽታ ግንባታ መጠቀም ይገባል ተባለ - መነሻ - am

Sisällytetyt portletit

Sisältöjulkaisija

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ pe, 17 kesäkuuta 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች ke, 8 kesäkuuta 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ ke, 8 kesäkuuta 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Sisältöjulkaisija

የናይል ተፋሰስ ሀገራት የሚሳተፉበት የሴካፋ ውድድሩ ለህዳሴው ግድብ ገጽታ ግንባታ መጠቀም ይገባል ተባለ

ኢትዮጵያ የምታዘጋጀው የናይል ተፋሰስ ሀገራት የሚሳተፉበት የሴካፋ ውድድሩ ለህዳሴው ግድብ ገጽታ ግንባታ መጠቀም እንደሚገባ ተገለጸ።

የምስራቅና የመካከለኛው አፍሪካ ሀገራት (ሴካፋ) ውድድር ቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተገምግሟል።

የቅድመ ዝግጅት ስራዎቹ የፌዴራል የስፖርት ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት 6 ንዑሳን ኮሚቴዎች የስራ ዝርዝር ቀርቦ በባህር ዳር ከተማ ነው የተገመገመው።

በግምገማው አስተናጋጁ የአማራ ክልል ተወዳዳሪ ሀገራትን ተቀብሎ ለማስተናገድ አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

በግምገማው ላይ የተገኙት የስፖርት ኮሚሽነር አቶ ኤሊያስ ሽኩር እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚደንት አቶ ኢሳያስ ጅራ እየተሰራ ያለው የቅድመ ዝግጅት ስራ በከፍተኛ ትኩረት ተይዞ እየተሰራ በመሆኑ ደስታቸውን ገልጸዋል።

ኃላፊዎች አያይዘውም በዚህ የሴካፋ ውድድር ላይ የናይል ተፋሰስ ሀገራት የሚሳተፉበት ትልቅ ትርጉም ያለው ውድድር በመሆኑ ከህዳሴው ግድባችን ስኬት ጋር በማያያዝ አጋጣሚውን ልንጠቅምበት እንደሚገባና በዚህም ቅኝት ውስጥ ሆነን ሁሉን አቀፍ የተቀናጀና ትርጉም ያለው ስራ ሊስራ እንድሚገባ በጥብቅ አሳስበዋል።

በተጨማሪም የመወዳደሪያና የመለማመጃ ሜዳዎችን በመመልከት የማስተካከያ ምክረ ሀሳቦችን መስጠታቸውን ከስፖርት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኤፍ ሰኔ 30 201

Sisällytetyt portletit

Sisältöjulkaisija