በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ዘለቄታዊ ጠቀሜታ ላይ ያተኮረ ፎረም በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተጀመረ - መነሻ - am
Portlets anidados
Publicador de contenidos
Statistics
× አድራሻ: ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስኩየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር
Búsqueda del contenido de Web
Publicador de contenidos
በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዘለቄታዊ ጠቀሜታ ላይ ያተኮረ ሃገራዊ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ መካሄድ ጀምሯል።
"የምሁራን ትብብርና ተሳትፎ ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዘለቄታዊ ጠቀሜታ" በሚል መሪ ሃሳብ በሚካሄደው ፎረም ላይ የሃገሪቱ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ምሁራንም እየተሣተፉ ነው።
በተጨማሪም በፎረሙ ላይ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሠር አፈወርቅ ካሱ ፣የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሣትፎ ማስተባበሪያ ምክርቤት ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አረጋዊ በርሄን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
ሃገራዊ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረሙ የሁለት ቀናት ቆይታ እንዳለውም መገለጹን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኤፍ.ቢ.ሲ
Portlets anidados
Publicador de contenidos
— Resultados por página