የህዳሴ ግድብ ግንባታ ሰራተኞችና ሃላፊዎች በእሳት የተፈተኑ የልማት አርበኞች ናቸው - ዶ/ር አረጋዊ በርሔ - መነሻ - am
Portlets anidados
Publicador de contenidos
Statistics
× አድራሻ: ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስኩየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር
Búsqueda del contenido de Web
Publicador de contenidos
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሰራተኞችና ሃላፊዎች በእሳት የተፈተኑ የልማት አርበኞች ናቸው ሲሉ የግድቡ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አረጋዊ በርሔ ገለጹ።
ኢትዮጵያ ለውጥ ውስጥ ከገባች ወዲህ መንግስት ግድቡን ለማጠናቀቅ በሙሉ አቅሙ እየሰራ እንደሆነም ተናግረዋል።
መንግስት በቁርጠኝነት በመስራት የግድቡ ግንባታ ሂደት ከነበረበት ውስብስብ ችግር ውስጥ ወጥቶ አሁን የሚያኮራ ደረጃ ላይ እንዳደረሰውም ገልጸዋል።
“በግድቡ ግንባታ ሂደት እየተሳተፉ የሚገኙ ሰራተኞችና የስራ ኃላፊዎች በእሳት የተፈተኑ የልማት አርበኞች ናቸው ማለት ይቻላል” ያሉት ዶክተር አረጋዊ፤ ሰራተኞችና ሃላፊዎች የአካባቢውን ከፍተኛ ሙቀት ተቋቁመው ያለ እረፍት እየሰሩ እንደሚገኙም ነው ያስረዱት።
ግድቡን በሚቀጥሉት ሁለትና ሶስት ዓመታት ውስጥ ለማጠናቀቅ እየተሰራ እንደሆነ ጠቁመው፤ ሁሉም ኢትዮጵያውያን እጅ ለእጅ በመያያዝ የጋራ አሻራቸው ያረፈበት ግድብ እስኪጠናቀቅ የሚያደረጉትን የገንዘብ፣ የእውቀትና የጉልበት ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ማስተላለፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ኤፍ ቢ ሲ
Portlets anidados
Publicador de contenidos
— Resultados por página