ሕዳሴ ግድብን ከደለል ለመታደግ የዓባይ ተፋሰስን በቆላ ቀርከሀ ለማልማት ስምምነት ተፈረመ - መነሻ - am
Portlets anidados
Publicador de contenidos
Statistics
× አድራሻ: ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስኩየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር
Búsqueda del contenido de Web
Publicador de contenidos
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ከደለል ለመታደግ የዓባይ ተፋሰስን በቆላ ቀርከሀ ለማልማት ተቋማት ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
ስምምነቱን የተፈራረሙት የአካባቢ ደን እና አየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን፣ የአካባቢና ደን ምርምር ኢንስቲትዩት፣ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ እና ሰላሌ ዩኒቨርስቲ ናቸው፡፡
በመጀመሪያ ዙር በቆላ ቀርከሀ ለማልማት የታሰበው የደጀን እና የጎሀጽዮን የዓባይ ተፋሰስ ቆላማ አካባቢዎችን ነው ተብሏል፡፡
የአካባቢና ደን ምርምር ኢንስቲትዩትም የቆላ ቀርከሀ ዛፍ ችግኞችን እያባዛ መሆኑን ገልጿል፡፡
እስካሁን ድረስ 10 ሺህ ችግኞችን ማባዛቱን ኢንስቲትዩቱ ጠቅሶ በቀጣይም 500 ሺህ ለማባዛት ማቀዱን ጠቁሟል፡፡
የቆላ ቀርከሀ የዓባይ ተፋሰስ በደለል እንዳይሞላ እና ሥነ-ምኅዳሩ እንዲያገግም ከማድረግ ባለፈ ለአካባቢው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡
Portlets anidados
Publicador de contenidos
— Resultados por página