Asset Publisher

የስፖት ውድድር ማስታወቂያ
የስፖት ውድድር ማስታወቂያ I. መግቢያ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ስራ በነበረው አደረጃጀት ሕዝብ እየተሳተፈበት እዚህ ደርሷል፡፡ ይሁን እንጂ ግድቡን ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በሚገባ ለማስተዋወቅ የነበረውን መደበኛ አሰራር ማዘመን አስፈልጓል፡፡ ምክንያቱም ኢፍትኃዊ የሆነው የግብጽ ድምጽ "ተሰሚነት" እያገኘ ዕውነት የያዘው ሕዝባችን ግን በያለበት ሲከፋ ቆይቷል፡፡ በመሆኑም ይህን በመቀየር ግድባችንን ጊዜው በሚፈቅደው መንገድ ለማስተዋወቅ `Internationalization of GERD` የሚል ዕቅድ በጽ/ቤቱ ተዘጋጅቷል፡፡ ይህን ወደ ተግባር ለማስገባት አጠቃላይ ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር `GERD NETWORK` የሚል ትስስር ተፈጥሯል፡፡ ትስስሩ መደበኛውን የመንግስት እንቅስቃሴና ዲፕሎማሲ የሚያግዝ ሕዝባዊ ትስስር ነው፡፡ ከመንግስት ድጋፍ ቢያገኝም በዋናነት የሕዝብ መሰባሰቢ፣ የሕዳሴ ግድብ የመከራከሪያና ድምፅ የማሰሚያ መድረክ እንዲሆን ታቅዷል፡፡ ትስስሩ ሶስት ዓላማዎች አሉት፡፡ • ሁሉንም ሞባይልና ኢንተርኔት ተጠቃሚ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆችን በአንድ የሶሻል ሚዲያ ገጽ ላይ ማሰባሰብ፣ • በወቅት የተለየ አጀንዳ በመፍጠር፣ ለዚህም ተገቢ መልዕክት በመቅረጽ፣ ለመልዕክቶቹ ሳቢ ፕሮዳክሽን በማዘጋጀት በትስስሩ ስር ላሉ ሚሊዮኖች በማስተላለፍ ወጥ ግንዛቤና አቋም ማስያዝ፣ • ወጥ አቋምና ግንዛቤ የያዙ ሚሊዮኖች መልዕክቶቹን እያባዙ ወደ ተመረጡ ግለሰቦች፣ ቡድኖች እና ተቋማት በመላክ በአጀንዳው ላይ ወዳጆችን ማበራከት፣ ተጽዕኖ መፍጠር ይህን ለማሳካት በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ ያሉ ተገቢ አካላት በበጎ ፈቃደኝነት ተሰባስበዋል፡፡ ትስስሩም በይፋ ተመስርቷል፡፡ ለግድቡ ሀብት ማሰባሰብ፣ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ መስራትና ደለል የመከላከል ስራ ማከናወን የትስስሩ ቋሚ ይዘቶች ሆነው ተለይተዋል፤ ተደራጅተዋል፡፡ እነኚህን ይዘቶች ወቅታዊነት እየለየ አጀንዳ የሚቀርጽ 16 አባላት ያሉት ዋና አስተባባሪ አካል ተለይቷል፡፡ ለአጀንዳው መልዕክት በመቅረጽና ፕሮዳክሽን በመስራት በፌስቡክ፣ በዩቱብ፣ በኢንስታግራም፣ በትዊተርና በቴሌግራም የሚያሰራጭ የበጎ ፈቃደኞች ቡድን ተደራጅቶ ወደ ስራ ገብቷል፡፡ የተሰራጩ መልዕክቶችንና ፕሮዳክሽኖችን በራሳቸው ትስስር ወደ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ትስስራቸው በማሰራጨት መሞገት እንዲችሉ የሲቪል ማህበራት፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የኪነጥበብ ባለሙያዎች፣ የኢትዮጵያ ወዳጆች፣ የመንግስት ሰራተኞች፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በዚህ ትስስር ውስጥ ተካተዋል፡፡ ይህ ትስስር በዋናነት በበጎ ፈቃደኛ ዜጎች የጊዜ፣ የዕውቀትና የሀብት አስተዋጽዖ የሚተገበር ነው፡፡ ይህ ውድድር በዚህ ትስስር የተዘጋጀ ነው፡፡ የትስስሩ ሞቶ “ጥምረት ለፍትህ” የሚል ነው፡፡ ዋና ዓላማውም በአባይ ወንዝ ላይ ፍትኃዊ ተጠቃሚነታችንን ለማረጋገጥ የፈጠርነው ጥምረት ስለሆነ ነው፡፡ እንደሚታወቀው የውሃው 86 ከመቶ አመንጪ ሀገር ኢትዮጵያ ናት፡፡ ውሃውን መቶ ከመቶ የሚጠቀሙበት አንድም ጠብታ ውሃ የማያመነጩት ግብጽና ሱዳን ናቸው፡፡ በውሃው ላይ በ1929 እና በ1959 ተደራድረው ሲካፈሉ ኢትዮጵያን አላማከሩም፡፡ ወንዙን በየሀገራቸው ሲገድቡ ኢትዮፕያን አላማከሩም፡፡ የወንዙን ውሃ ከመስመሩ አውጥተው ወደ በረሃ ሲወስዱ ኢትዮጵያን አላማከሩም፡፡ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ለኃይል ማመንጫ ነው ምትገድበው፡፤ ይህ ማለት ውሃው ኃይል አመንጭቶ፣ ያውም አመቱን ሙሉ በመደበኛነት መፍሰሱን ይቀጥላል ማለት ነው፡፡ ኢትዮጵያ ይህንንም ስትሰራ እንዲያውቁት አድርጋለች፡፡ በቴክኒካል ጉዳይ ላይ ለመደራደርም ዝግጁ ናት፡፡ ግብጽ ግን በዓለም አቀፍ መድረክ ጭምር እየከሰሰቻት ነው፡፡ ጦር ሰብቃ እየዛተችባት ነው፡፡ የውስጥ ፖለቲካዋ ውስጥ ገብታ እያፋጀቻት ነው፡፡ ለምን ቢባል “ምንም ቢጠማሽ ውሃሽን መጠቀም የምችለው እኔ ብቻ ነኝ” ነው የምትለው፡፡ “ኢትዮጵያውያን በረሃብ፣ በጥማትና በጨለማ ቢሰቃዩም ውሃውን አባካኝ በሆነ መንገድም ቢሆን እንዳሻኝ እንዳደርገው አግዙኝ” ብላ ነው ወደ ዓለምዓቀፉ ዲፕሎማሲ የሄደችው፡፡ ደግፈዋት የታዩ ሀገራት የደገፉት ይህን የለየለት ራስ ወዳድነት ነው፡፡ በመሆኑም ውድድሩ በየደረጃው ያሉ ዜጎች ይህን ምን አልባትም በዓለም የዲፕሎማሲ ታሪክ “ዓይን አውጣ ክርክር” ሊባል የሚችል ኢፍትኃዊ የግብጽ ክርክር የሚሞግቱበት ዕድል መፍጠር ነው፡፡ በዩቱብ እና በቲክ ቶክ ላይ ለተዓምር የቀረበ ፈጠራ ሲሰሩ ለምናያቸው ወጣቶች በዚህ የክ/ዘመኑ የዲፕሎማሲ ቀልድ ላይ ለዓለም የሚሆን መልዕክት እንዲያስተላልፉ ዕድል ማመቻቸት ነው፡፡ II. የውድድሩ መስፈርቶች 1. የውድድሩ ዓይነት፡- ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ ትስስር ገፆች የሚሆን ስፖት፣ ግጥም፣ የካርቱን ሥራ፣ አኒሜሽን፣ 2. የውድድር ሥራዎቹ ይዘት፡ • የኢትዮጵያ ፍትኃዊ ጥያቄና የግብፅ ኢፍትኃዊ ክርክርን የሚሞግት፣ የሚያጋልጥ፣ የሚያሳይ ሆኖ በይዘትም ሆነ በአቀራረብ፣ o በግለሰቦች ወይም በድርጅቶች ላይ ቀጥተኛ ጥቃትና ሁከት የማይቀሰቅስ፣ ጸያፍ መልዕክት የማያስተላልፍ፣ ከማህበረሰቡን ተለምዷዊ ህጎች የማይጋጭ፣ የጾታ የሃይማኖትና የብሔር እኩልነትን የሚያከብር፣ በአማርኛ ቋንቋ የሚቀርብ ይሆናል፡፡ 3. የውድድር ሥራዎቹ ልኬት፣ • ስፖት፡ ርዝማኔ ከ45-60 ሰከንድ፣ Resolution (HD (High Definition)), Pixel Size (1280 x 720), Aspect Ratio (16:9) • ግጥም፣ ከ6 - 10 መስመር • የካርቱን ስዕል ይዘቶች፤ JPEG/PNG/PDF, high quality (preferably 300 dpi) • አኒሜሽን: 3D፣ርዝማኔ ከ30-40 ሰከንድ፣ Resolution (HD (High Definition)), Pixel Size (1280 x 720), Aspect Ratio (16:9) • ሁሉም ስራዎች ለአብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል መረዳት የቀረቡ፣ ቀላል ሳቢ ማራኪና ገላጭ፣ ከሌላ ያልተወሰዱና ከዚህ በፊት ለየትኛውም ሚዲያ ያልቀረቡ 4. ተወዳዳሪዎች ማንኛውም የሕብረተሰብ ክፍል፣ (ኢትዮጵያዊ፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊና የኢትዮጵያ ወዳጆች፣ በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጪም የሚኖሩ) መሳተፍ ይችላሉ 5. ለውድድር መነሻ ሀሳብ የሚሆኑ ሰነዶች፤ ተወዳዳሪዎች የራሳቸውን ዕውቀትና ምልከታ መጠቀም እና ባለፉት ዓመታት የነበሩ የዲፕሎማሲ ሂደቶችን መጠቀም ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም በትስስሩ ገፆች ላይ ለዚሁ ተብለው የተለጠፉ አጫጭር ሰነዶችን መጠቀም ይችላሉ፤ 6. ባለቤትነት፡ በውድድሩ አሸናፊ የሆኑ ስራዎች የመጠቀም መብት የጽ/ቤቱ ይሆናል፡፡ አሸናፊ ያልሆኑና የምስክር ወረቀት ያገኙ ስራዎችንም ጽ/ቤቱ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በሕዳሴ ግድብ ትስስር ገጾች ላይ ሊጠቀምባቸው ይችላል፡፡ 7. የስራዎቹ ማስረከቢያ ቀናት፡ • ለሁሉም ስራዎች ማስረከቢያ ቀን የውድድር ማስታወቂያው በዓየር ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ (ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ) ባሉት 15 ቀናት ውስጥ • ለአሸናፊ ሥራዎች ውጤት ማሳወቂያ ቀን የማስረከቢያ ቀናት ባለቀ በ10 ቀናት ውስጥ ገለጻል፣ 8. የውድድር ስራዎች ገቢ የሚሆንበት መንገድ ሁሉም ስራ