የታላቁ ህዳሴ ግድብ አጭር የፅሁፍ መልዕክት የገቢ ማሰባሰቢያ 3ኛ ዙር ሁለተኛ ተሸላሚ መኪናቸውን ተረከቡ - መነሻ - am
Verschachtelte Portlets
Asset Publisher
Statistics
× አድራሻ: ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስኩየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር
Webcontentsuche
Asset Publisher
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 12፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የታላቁ ህዳሴ ግድብ አጭር የፅሁፍ መልዕክት የገቢ ማሰባሰቢያ የ3ኛ ዙር ሁለተኛ ተሸላሚ መኪናቸውን ተረከቡ፡፡
አሸናፊዋ ወይዘሮ አሰፋሽ አፈወርቅ ከኢሉባቡር በቾ ወረዳ ሲሆኑ ዘመናዊ ቢዋይ ዲ መኪና ተረክበዋል።
የስልክ መልዕክት የገቢ ማሰባሰቢያው የተጀመረው ባሳለፍነው አመት የካቲት ወር ላይ ሲሆን÷ በዚህም ከ67 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉ ተገልጿል።
በርክክብ ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የቀድሞ የምድር ጦር ሰራዊት አባላትና የሲቪል ሰራተኞች ማህበር የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ አባላት ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል የ10 ሺህ ብር ስጦታ አበርክተዋል።
ስጦታውን ያስረከቡት የቀድሞ የምድር ጦር ሰራዊት አባላት ድጋፋቸው ቀጣይ እንደሚሆንና ሁሉም ባለው አቅም ለህዳሴ ግድብ አሻራውን እንዲያኖር ጥሪ አቅርበዋል።
የግድቡ የመጀመሪያው የውሃ ሙሌት ከተካሄደ በኋላ የህዝቡ ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉም በዚህ ወቅት ተገልጿል።
በመስከረም ወር ብቻም ከ197 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉና ይህም ከእስካሁኑ ከፍተኛ መሆኑ ተጠቁሟል።
Verschachtelte Portlets
Asset Publisher
— 5 Elemente pro Seite