ሱዳን ከግድቡ ጋር ተያይዞ ላሉ ልዩነቶች የአፍሪካ ህብረት መፍትሄ እንደሚሰጥ እምነቷ መሆኑን ገለፀች - መነሻ - am

Verschachtelte Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fr, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Mi, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Mi, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

ሱዳን ከግድቡ ጋር ተያይዞ ላሉ ልዩነቶች የአፍሪካ ህብረት መፍትሄ እንደሚሰጥ እምነቷ መሆኑን ገለፀች
በኢትዮጵያ ከታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ጋር ተያይዞ ያሉ ልዩነቶች በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ይፈታሉ የሚል ጠንካራ እምነት እንዳላት ሱዳን ገለፀች።
በህዳሴ ግድብ ዙሪያ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ውጤታማ እና ፈጣን መፍትሄ ላይ እንደሚደረስ እምነቷ መሆኑንን አስታውቃለች።
ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ በሚለው መሪ ቃል የሶስትዮሽ ድርድሩ እንዲቀጥል ፍላጎት እንዳላትም ነው ሱዳን የገለፀችው።
የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ወሳኙን እና አዲስ ሃሳብና አሰራር የሚመጣበትን የአፍሪካ ህብረትን እንደሚያደንቅ መግለፁን ሱና ዘግቧል።
ከዚህ ጋር ተያይዞም ሱዳን አቋሟን ለማስረዳት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ የሚመራ ልዑክ ወደ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፣ ኬንያ ፣ ሩዋንዳ እና ኡጋንዳ እንደምትልክ ገልጻለች።
ኤፍ ቢ ሲ

Verschachtelte Portlets

Asset Publisher

— 5 Elemente pro Seite
Zeige 1 - 5 von 16 Ergebnissen.