ግድቡ የእናቶችን ችግር የሚቀርፍ በመሆኑ ታላቅ ህዝባዊ ተሳትፎዎች ለመፍጠርና ግድቡን ለማጠናቀቅ ዝግጁ መሆናቸውን ዶ/ር አረጋዊ አስታወቁ - መነሻ - am
Mòduls de portal imbricats
Editor de continguts
Statistics
Cerca de contingut web
Editor de continguts
ግድቡ የእናቶችን ችግር የሚቀርፍ በመሆኑ ታላቅ ህዝባዊ ተሳትፎዎች ለመፍጠርና ግድቡን ለማጠናቀቅ ዝግጁ መሆናቸውን ዶ/ር አረጋዊ አስታወቁ
- ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ወደ ሹመት መምጣታቸው ትልቅ አገራዊ ለውጥ ነው ብለዋል
ግድብ የእናቶቻችንን ችግር የሚቀርፍ በመሆኑ ታላቅ ህዝባዊ ተሳትፎዎች ለመፍጠርና ግድቡን ለማጠናቀቅ ዝግጁ መሆናቸውን ዶ/ር አረጋዊ በርሄ አስታወቁ።
ዶ/ር አረጋዊ በርሔ በዛሬው ዕለት ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ሆነው በመሾማቸው ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸዋል፡፡
የምክር ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አረጋዊ በርሄ ዛሬ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ያሉበትን ችግሮች በመቅረፍና ታላቅ ህዝባዊ ተሳትፎዎች እንዲኖሩ በማድረግ በቁርጠኝነት ለመስራት ዝግጁ ናቸው፡፡
በህዳሴው ግድብ ላይ ህዝባዊ ንቅናቄው የላቀ ተሳትፎ እንዲኖረው ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል ባሳተፈ መልኩ የተለያዩ ሥራዎችን ለመስራት ዕቅድ እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡
የህዳሴውው ግድብ በይበልጥ የእናቶቻችንን ችግር የሚቀርፍ ነው ያሉት ዶ/ር አረጋዊ፤ ይህንን እና መሰል የግድቡን ቱሩፋቶች ከግምት ውስጥ በማስገባት የተሰጠኝን ሀላፊነት በትጋት እወጣዋለሁም ብለዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ወደ ሹመት መምጣታቸው ትልቅ አገራዊ ለውጥ መሆኑንም ዶ/ር አረጋዊ ተናግረዋል።
ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች አሁን ላይ ወደ ሹመት እየመጡበት ያለው መንገድ በአውንታዊ ሊታይ የሚችል ነው ያሉት ዶክተሩ፤ አሁን ላይ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ሁሉም ባለው ችሎታ እየተመዘነ ሀገሩን ሊያገለግል የሚችልበት እድል መሰጠቱ የለውጡ አንድ በጎ መገለጫ ነው ብለዋል፡፡
መንግስት ከዚህ በፊትም ለፓሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተርነት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስን መሾሙ ይታወሳል።
(ኢ.ፕድ)