ታላቁ የህዳሴ ግድብ የቀጠናዉን ምጣኔ ሃብታዊ ትስስር በማጠናከር ለሰላም ያለዉ ዋጋ ከፍተኛ ነው ተባለ - መነሻ - am
Mòduls de portal imbricats
Editor de continguts
Statistics
Cerca de contingut web
Editor de continguts
ታላቁ የህዳሴ ግድብ የቀጠናዉን ምጣኔ ሃብታዊ ትስስር በማጠናከር ለሰላም ያለዉ ዋጋ ከፍተኛ መሆኑን የዘርፉ ተመራማሪዎች ተናገሩ ፡፡
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የቀድሞ የህዳሴ ግድብ ተደራዳሪ እና የአባይ ጅኦ ፓለቲካ ጉዳይን በቅርበት የሚከታተሉት አቶ ፈቅ አህመድ ነጋሽ÷ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችን ተከትሎ የተነሳ የጦርነት የቅርብ ታሪክ አለመኖሩን ያስረዳሉ ፡፡
የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችን ተከትሎ በሃገራት መካከል ፍጥጫና ትብብሮች መሳ ለመሳ ይሄዳሉ የሚሉት አቶ ፈቅ÷ ይህ የተለመደ የዉሃ ጅኦ ፖለቲካዊ አካሄድ ወደ ጦርነት የሚያመራ እንዳልሆነም አብራርተዋል ፡፡
ኢትዮጵያ እየገነባች የምትገኘዉ ታላቁ የህዳሴ ግድብ በተፋሰሱ ሃገራት ዉስጥ የመጀመሪያ እንዳልሆነ የሚያነሱት ተመራማሪው÷ ግብጽ ከህዳሴዉ ግድብ ከሁለት እጥፍ በላይ ዉሃ የመያዝ አቅምያለዉን የአስዋን ግድብ እንኳን በቀጠናዉ ሰላም ላይ አሉታዊ ሚና ሲፈጥር እንደማይስተዋልም ጠቁመዋል፡፡
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የዉሃ ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት ሳይንሳዊ ዳይሬክተር ዶክተር አብደላ ከማል ÷ ታላቁ የህዳሴ ግድብ በየትኛዉም መመዘኛ ቀጠናዉን ወደ አለመረጋጋት ሊያመጣ አይችልም ብለዋል ፡፡
ይህ ፕሮጀክት በተቃራኒዉ ቀጠናዊ የምጣኔ ሃብት ትስስር እንዲጎለብት እና ወንድማማችነት እንዲያድግ የሚያግዝ እንደሆነ ተናግረዋል ፡፡
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት ምሁራኑ ፣ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ሱዳንን በየጊዜዉ ቀዉስ ዉስጥ እየከተታት ከሚገኘዉ የጎርፍ ችግር በመታደግ ና ለአህጉሩ ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችን በማምጣት ሚና እንደሚኖረዉ አብራርተዋል ፡፡
በጠንካራ የልማት ስራዎች ላይ በማተኮር የሃገሪቱን ምጣኔ ሃብት ማሳደግ እና የድርድር አቅምን ከፍ ማድረግ እንደሚጠበቅም ምሁራኑ ተናግረዋል ፡፡
ኤፍ ቢ ሲ፣ ሐምሌ 1 ፣ 2013