ለሕዳሴ ግድቡ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ አስታወቁ፡፡ - መነሻ - am

Mòduls de portal imbricats

Editor de continguts

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ dv., 17 de juny 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች dc., 8 de juny 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ dc., 8 de juny 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Editor de continguts

ለሕዳሴ ግድቡ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ አስታወቁ፡፡

በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ለሕዳሴ ግድቡ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው መቀጠላቸውን አምባሳደር ፍጹም አረጋ አስታውቀዋል፡፡ አምባሳደሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት እንዳሉት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ብርሃን ለመስጠት በተቃረበበት ወቅት ከአሜሪካ የወገን ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል::
ለረጅም ጊዜ የቦስተን ነዋሪ የሆኑት አቶ ሰለሞን ለማ ከቤተሰባቸው ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ በኤምባሲው ተገኝተው 4ሺህ የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ አድርገዋል ነው ያሉት፡፡ 3ሺህ የአሜሪካ ዶላሩ በቦንድ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡
በግሬተር ፊለደልፊያ ነዋሪ የሆኑ ወገኖች በድምሩ 7ሺህ 400 የአሜሪካን ዶላር መለገሳቸውንም ገልጸዋል:: እስካሁን የተሰበሰበው ግማሽ ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወደ ሀገር ቤት ተላልፏልም ብለዋል አምባሳደሩ፡፡
ምንጭ፡- አሚኮ

Mòduls de portal imbricats

Editor de continguts

— 5 articles per pàgina
S'estan mostrant 1 - 5 de 16 resultats.